Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ብሪታኒያ በትብብር መስራት የሚችሉባቸውን ጉዳዮች በመለየት ድጋፍ እናደርጋን-የብሪታኒያ አምባሳደር

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ በኢትዮጵያ ከብሪታኒያ አምባሳደር ዶክተር አላሰቴይር ማክፌይልን ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይቱ ዶክተር  በለጠ ኢትዮጵያና ብሪታኒያ የረጅም ዘመናት የቆየ ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው መሆኑን አውስተው ይህን ግንኙነት የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጡ መስክች ማጠናከርና ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸውላቸዋል።

በተለይም እንግሊዝ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን መስክ የካበተ ልምድና እውቀት ከሚገኝባቸው አገራት አንዱ እንደሆነ የጠቆሙት ሚኒስትሩ በዘርፉ ያለውን የዳበረ ልምድ ለኢትዮጵያ ለማጋራት የሚደረጉ ድጋፎችና ትብብሮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል፡፡

በሌላ በኩል መንግስት በአገራዊ ሁኔታው ላይ ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት አበክሮ እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

አምባሳደር ዶክተር አልሰቴር ማክፌይል በበኩላቸው አገራቱ ያላቸውን በመልካም የሚጠቀስ ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው ጠቁመው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ የልማት እና ትብብር ድጋፎችን ስታደርግ መቆየቷን አውስተዋል።

ወደፊትም መተባበር የሚቻልባቸውን ዘርፈ ብዙ ጉዳዮችን በመለየት ድጋፍ ለማድረግ እንሰራለን ማለታቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም የአገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ በትኩረት እየተከታተሉት እንዳለ የጠቆሙት አምባሳደሩ፤ ሁኔታው በአገራዊ የምክክር መድረክ ሊፈታ የሚችልበት እድል እንደሚፈጠር ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡

በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር አገራቸው በቀጣይ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ድጋፍ እንደምታደርግ ጠቅሰው በሌሎች የትብብር ዘርፎችም በመተባበር መስራት እንደሚገባ መክረዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.