Fana: At a Speed of Life!

የቅዱሱ ሚካኤልን ዝክር ለጭና ተፈናቃዮች የሰጡት የጎንደር ከተማ ነዋሪ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 03 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አቶ አያናው ጎነጠ በጎንደር ከተማ የአዘዞ ክፍለ ከተማ ነዋሪ ናቸው። መተዳደሪያቸው የጥበቃ ስራ ሲሆን፥ በየዓመቱ ህዳር 12 የሚከበረውን የመላኩ ቅዱስ ሚካኤል በዓል ለፍቅራቸው መግለጫ በስሙ ይዘክራሉ።
 
ሀገር ሰላም በሆነችበት ወቅት ለ”ፀበል ቅመሱ” የሚጠሩ የአካባቢው ነዋሪዎች በግለሰቡ ቤት ተገኝተው የተዘጋጀውን ፀበል ቀምሰው የዛሬ ዓመት በሰላም ያድርስልን ብለው መረቀው ይለያዩ ነበር።
 
ዘንድሮ የኢትዮጵያ ጠላቶች በአገራችን ላይ በከፈቱት ጦርነት ሳቢያ በርካታ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ስፍራ ይገኛሉ።
ይህ ጉዳይ ያሳሰባቸው አቶ አያናው፥ ለፍቅራቸው መግለጫ በየዓመቱ በቅዱስ ሚካኤል ስም የሚጠሯቸውን ሰዎች እንደተለመደው በቤታቸው ለመጥራት አልፈቀዱም። ከዛ ይልቅ ለድግሱ የሚያወጡትን 1 ሺህ 500 ብር ለጭና ተፈናቃዮች ለመስጠት ወስነዋል።
 
በርካታ ተፈናቃዮች በችግር ውስጥ ሆነው ህይወታቸውን እየመሩ በመሆኑ ሁሉም ሰዎ ይህን ህመም በመጋራት ለተቸገሩ ወገኖች ሊደርስላቸው ይገባል ይላሉ ባለታሪካችን።
 
“የዛሬ ዓመት ይህን ችግር አልፈን በሰላም ሀገር ስትረጋጋች የቅዱስ ሚካኤልን ቀን በተሻለ መንገድ እናከብረዋለን” የሚሉት አቶ አያናው፥ በተለያዩ ምክንያቶች ድግስ ለማዘጋጀት ያሰብን ካለን ለወገን እንድረስ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።
 
ምናለ አየነው
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.