Fana: At a Speed of Life!

የፍትህ ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ

 

አዲስ አበባ፣ህዳር 3፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፍትህ ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና በህልውና ዘመቻው ለተጎዱ ወገኖች ደም ለግሰዋል፡፡

ደም የመለገስ መርሃ ግብሩ የህልዉና ዘመቻዉ ከተጀመረ የአሁኑ ለ3ተኛ ጊዜ የተከናወነ ሲሆን÷ በፍትህ ሚኒስቴር የመንግስት ህግ እና ፍትህ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አለም አንተ አግደዉ በአሁኑ ወቅት የዉስጥና የዉጭ ሀይሎች በአገራችን የደቀኑትን አደጋ ተከትሎ መንግስት ያቀረበዉን ጥሪ በመቀበል ዜጎች በእልህና በወኔ ተንቀሳቅሰዋል ብለዋል፡፡

በህልውና ዘመቻው የሚጎዱ ወገኖችን ለመደገፍ ከእያንዳንዳችን የሚጠበቅ ትንሹ መስዋእትነት ደም በመሆኑ ለመከላከያና ለጸጥታ አካላት ያለንን አለኝታነት ለማሳየት የደም ልገሳ አከናውነናል ሲሉ መናገራቸውን ከፍትህ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.