Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተውን የሐሰት ዘመቻ የሚወግዝ ሰልፍ በካናዳ ቶሮንቶ ይካሄዳል

 

አዲስ አበባ፣ህዳር 3፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አንዳንድ ምዕራባውያን አገራትና መገናኛ ብዙሃኖቻቸው በኢትዮጵያ ላይ የከፈቱትን የሐሰት መረጃ የማሰራጨት ዘመቻ የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ ማምሻውን በካናዳ ቶሮንቶ ይካሄዳል ተባለ፡፡

ሰልፉ ዛሬ በኢትዮጵያውያን ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ ሶስት ጀምሮ በካናዳ ቶሮንቶ በሚገኘው የአሜሪካ ቆንስላ እንደሚካሄድ “የኢትዮጵያውያን ማህበር በቶሮንቶና በአካባቢው” አባል ጋዜጠኛ ብርሃኑ ተክለሚካኤል ተናግሯል፡፡

በሰልፉ ላይ ሀምሊተን፣ሚሲሳጋ፣ራምፕተን፣አጃክስ፣ስካርብሮ፣ኪቺነርና በሌሎች የካናዳ ከተሞች የሚኖሩ ዳያስፖራዎች በሰልፉ ላይ ለመሳተፍ ቶሮንቶ መግባታቸውንም ገልጿል።

ሰልፈኞቹ አሜሪካ፣ካናዳ እና ሌሎች ምዕራባውያን አገራት መገናኛ ብዙሃኖቻቸውን ተጠቅመው በኢትዮጵያ ላይ የከፈቱትን የሐሰት መረጃ ዘመቻ እንዲያቆሙ ጥሪ ያቀርባሉ ተብሏል።

ምዕራባውያን አገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ያልተገባ ጫና እና ጣልቃ ገብነት እንዲያቆሙ መልዕክታቸውን እንደሚያስተላልፉም ነው ጋዜጠኛ ብርሃኑ የገለጸው።
በተለይም የአሜሪካ መንግስትን ጣልቃ ገብነትን እንዲያቆም የሚጠይቅ ደብዳቤ በካናዳ ለሚገኘው የአሜሪካ ቆንስላ እንደሚሰጥም አመልክቷል።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በካናዳ የሚገኙ የኢትዮጵያ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ተወካዮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው ንግግር እንደሚያደርጉም ነው ኢዜአ የዘገበው።

በሰልፉ ዳያስፖራው የአገር ሕልውና ዘመቻውን በመደገፍ ከመንግስት ጎን መቆሙን የሚያሳይበት እንደሆነም ጋዜጠኛ ብርሃኑ አክሏል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.