Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር እና አልማ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ

 

አዲስ አበባ፣ህዳር 3፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በሽብርተኛው ህወሓት ምክንያት ከወሎ ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን ከተማ ለተጠለሉ ወገኖች የ3 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የምግብ ድጋፍ አድርጓል፡፡

በተመሳሳይ በአዲስ አበባ የየካ ክፍለ ከተማ የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) ከአባላቱና ከደጋፊዎቹ ሀብት በማሰባሰብ ከ3 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ምግብና ቁሳቁስ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አድርጓል፡፡

የፈረንሳይ ለጋሲዮን ወጣቶች እና በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ በማድረግ መሳተፋቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ታደሰ ገብረጻዲቅ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው ወደፊትም ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.