Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተውን የሀሰተኛ መረጃ ዘመቻ የሚቃወም ሰልፍ በቶሮንቶ ከተማ እየተካሄደ ነው

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 03 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምዕራባውያን አገራትና መገናኛ ብዙሃኖቻቸው በኢትዮጵያ ላይ የከፈቱትን የሐሰት መረጃ ዘመቻ የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በካናዳ ቶሮንቶ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው።

በቶሮንቶና በአካባቢው የኢትዮጵያውያን ማህበር አባል የሆነው ጋዜጠኛ ብርሃኑ ተክለሚካኤል፥ የተቃውሞ ሰልፉ በካናዳ ቶሮንቶ በሚገኘው የአሜሪካ ቆንስላ በር ላይ እየተካሄደ መሆኑን ለኢዜአ ገልጿል ።

በሰልፉ ላይ በሀምሊተን፣ሚሲሳጋ፣ራምፕተን፣ አጃክስ፣ ስካርብሮ፣ ኪቺነር እና በሌሎች የካናዳ ከተሞች የሚኖሩ አትዮጵያውያንና ትውልደ አትዮጵያውያን በሰልፉ ላይ ተሳታፊዎች ናቸው።

ሰልፈኞቹ አሜሪካ፣ ካናዳ እና ሌሎች ምዕራባውያን አገራት መገናኛ ብዙሃኖቻቸውን ተጠቅመው በኢትዮጵያ ላይ የከፈቱትን የሐሰት መረጃ ዘመቻ በመቃወም ከድርጊታቸው እንድታቀሙ በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡

ምዕራባውያን አገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ያልተገባ ጫና እና የውስጥ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆሙ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እያሰሙ መሆናቸውን ጋዜጠኛው ገልጿል፡፡

ጋዜጠኛ ብርሃኑ በተለይም የአሜሪካ መንግስትን ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም የሚጠይቅ ደብዳቤ በካናዳ ለሚገኘው የአሜሪካ ቆንስላ እንደሚሰጥ አመልክቷል።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በካናዳ የሚገኙ የኢትዮጵያ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ተወካዮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው ንግግር እንደሚያደርጉም ይጠበቃል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.