Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ሕወሓት ከመሰረቱ በውሸት የተካነ ነው – ኢ/ር ግደይ የሕወሓት መስራችና አንጋፋ ፖለቲከኛ

አዲስ አበባ፣ህዳር 4፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ሕወሓት ከመሰረቱ በውሸት የተካነ ቡድን መሆኑን የሕወሓት መስራችና አንጋፋው ፖለቲከኛ ኢንጅነር ግደይ ዘረዓጽዮን ገለጹ፡፡
የሕወሓት መስራችና አንጋፋው ፖለቲከኛ ኢንጅነር ግደይ ዘረዓጽዮን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፥ አሸባሪው ሕወሓት ከመሰረቱ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ተወልዶ ያረጀበትን የሐሰት ድራማ እየሰራ ለሚዲያ ፍጆታ የሚያውል ቡድን ነው፤ ከአፈጣጠሩም በውሸት የተካነ ነው ብለዋል፡፡
ከአሸባሪ ቡድኑ ጋር የወገኑ የውጭ ኃይሎችም የቡድኑን የሐሰት መረጃዎች ተቀብለው ሲያስተጋቡላቸው እንደቆዩ አውስተው ፥ ከእነዚህ የሐሰት መረጃዎች መካከልም በትግራይ ክልል የዘር ማጥፋት እንደተፈጸመ ቡድኑ ሲነዛው የነበረው የሐሰት መረጃ አንዱ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡
ይህ መሰረተ ቢስ ወሬ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጽህፈት ቤት በጣምራ ባወጡት ሪፖርት ሐሰት መሆኑ ተረጋግጧል ብለዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
May be an image of 1 person and sitting
69
People reached
1,374
Engagements
Distribution score
Boost post
461
42 Comments
29 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.