Fana: At a Speed of Life!

ኢሰመኮ ህወሓት በሰሜን ወሎና ደቡብ ጎንደር ዞኖች ንጹሃንን በመግደል የንብረት ዘረፋና ውድመት መፈጸሙን አረጋግጫለሁ አለ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ታጣቂ ቡድን በአማራ ክልል ሰሜን ወሎና ደቡብ ጎንደር ዞኖች ንጹሃንን መግደሉንና ሆን ብሎ የንብረት ዘረፋና ውድመት እንደፈጸመ ማረጋገጡን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ዛሬ ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል።
የተፈጸሙ ጥሰቶች የጦር ወንጀል ስለመሆናቸው አመላካች ሁኔታዎች እንዳሉም ኮሚሽኑ ገልጿል።
ኮሚሽኑ ከሐምሌ ወር 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በትግራይ ክልል የነበረው ጦርነት ወደ አማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ከመስፋፋቱ ጋር ተያይዞ በሕወሓት ኃይሎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት እና የሰብአዊነት ሕግ ጥሰቶችን በተመለከተ ያደረገውን ምርመራ ሪፖርት ነው ዛሬ ይፋ ያደረገው።
ከሰኔ 21 ቀን እስከ ነሃሴ 22 ቀን 2013 ዓ.ም ባለው ጊዜ የሚሸፍነው ይህ ሪፖርት እስከ ነሃሴ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በተካሄደ ምርመራ 128 ቃለመጠይቆችን፣ ከተጎጂዎችና ቤተሰቦቻቸው፣ ከአካባቢው ነዋሪዎች፣ የሲቪል እና የፀጥታ አካላት፣ ከሲቪክ ማኅበረሰብ አባላት፣ ከተራድኦ ድርጅቶች ጨምሮ 21 የቡድን ውይይቶችን አድርጓል።
ኮሚሽኑ በሪፖርቱ እንዳመላከተው ምርመራው ባተኮረባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች በተደረገው ጦርነት ቢያንስ የ184 ንጹሃን ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ እንዲሁም በርካታ ሰዎች የአካል ጉዳት እና የሥነ ልቦና ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል።
በተለይ የሕወሓት ታጣቂዎች በቁጥጥራቸው ስር በገቡ ከተሞች እና ገጠራማ አካባቢዎች ንጹሃን ሰዎችን ተኩሰው መግደላቸውንና ማቁሰላቸውን፣ ሰፊ የንብረት ዘረፋ እና ውድመት ሆን ብለው መፈፀማቸውን አረጋግጧል።
እንዲሁም የሕወሓት ኃይሎች ወደ ከተሞች ከባድ መሳሪያዎችን መተኮሳቸውን፣ በንጹሃን ሰዎች መኖሪያ ቤቶች እና ቅጥር ግቢዎች ውስጥ ምሽግ በመቆፈር እና ከባድ መሳሪያዎችን በመተኮስ ንጹሃን ዜጎችን በአፀፋ ለሚተኮሱ ከባድ መሳሪያዎች ጥቃት ማጋለጣቸውንም ነው የገለጸው ሪፖርቱ።
በዚህ ሳቢያም በበርካታ ሲቪል ሰዎች ሞት እና አካል ጉዳት እንዲከሰት እንዲሁም ንብረት እንዲወድም ምክንያት መሆናቸውን ሪፖርቱ አመላክቷል።
አካባቢህን ጠብቅ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
May be an image of text that says 'የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ETHIOPIAN HUMAN RIGHTS COMMISSION'
0
People reached
6
Engagements
Distribution score
Boost post
6
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.