Fana: At a Speed of Life!

ፖሊስ አዳዲሶቹን የደንብ ልብሶች አስመስሎ መጠቀም ፍፁም ክልክል መሆኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ነባሩን በመተካት ሥራ ላይ ያዋላቸውን ሦስት ዓይነት የደንብ አልባሳት አስመስሎ መጠቀም ፍፁም ክልክል መሆኑን አስታውቋል።
በአገር አቀፍ ደረጃ የፖሊስ ተቋማትን ለማዘመን በተያዘው ስትራቴጂካዊ እቅድ የፖሊስ ሠራዊት አርማ እና የደንብ ልብስ እንዲቀየር በተወሰነው መሰረት የአዲስ አበባ ፖሊስ አዲስ አርማና የደንብ ልብስ ስራ ላይ ማዋሉ ይታወቃል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኦሞ ሸሚዝ በጥቁር ሰማያዊ ሱሪ ከነ መለዮው፣ ካኪ ሱሪ እና ሸሚዝ በቦኔት መለዮ የደንብ ልብስን ለመደበኛ የፖሊስ ስራ እንዲሁም ቡራቡሬ ወይም ሬንጀር መልክ ያለው ለቋሚና ተወርዋሪ ኃይል የሚጠቀም መሆኑን ገልጿል።
አዲስ ስራ ላይ የዋለውን ወይም ከሌሎች የፀጥታ አካላት የደንብ ልብስ ጋር ተመሳሳይ ወይም ተቀራራቢ ዩኒፎርም መጠቀም ክልክል ነው ማለቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያመላክታል።
ከአዲስ አበባ ፖሊስ የደንብ ልብስ ጋር ተመሳሳይ ዩኒፎርም የሚጠቀሙ አካላት ማስተካከያ እንዲያደርጉ እያሳሰበ ከዚህ ቀደም ሲጠቀምበት የነበረው ነባሩ የደንብ ልብስ አገልግሎት የማይሰጥ መሆኑንም ገልጿል።
አካባቢህን ጠብቅ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.