Fana: At a Speed of Life!

የጌዲኦ ዞን ነዋሪዎች ለአምስተኛ ጊዜ ለህልውና ዘመቻው ስንቅ አዘጋጁ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጌዲኦ ዞን እናቶች ለአምስተኛ ጊዜ በህልውና ዘመቻው እየተሳተፉ ላሉ ጀግኖች ግምቱ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ ስንቅ አዘጋጁ፡፡
የህይወት መስዋዕትነት የሚከፍለውን የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የተለያዩ የፀጥታ ሀይሎችን እኛ ማድረግ በምንችለው ሁሉ የመደገፍ ግዴታ አለብን ያሉት በዞኑ የሚገኙ እናቶች÷ በዛሬው ዕለትም በዲላ ከተማ ስንቅ በማዘጋጀት አጋርነታቸውን አሳይተዋል፡፡
የዛሬው ድጋፍ ለአምስተኛ ጊዜ የተደረገ መሆኑን የገለፁት የዞኑ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ እቴነሽ በየነ÷ ድጋፉን አጠናክሮ ለመቀጠል ማህበረሰቡ ዘንድ ጥሩ ተነሳሽነት መስተዋሉን አመልክተዋል።
የዛሬው የስንቅ ዝግጅት በገንዘብ ሲተመን ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ መሆኑም ተገልጿል፡፡
በተያያዘም ወደ ጦር ግምባር ለሚሄዱ የጌዴኦ ዞን አመራሮችና ተጠባባቂ ሃይሎች ሽኝት ተደርጓ፡፡
በሽኝት መርሃ ግብሩም÷ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዮት ደምሴ ሀገራችን የመሸነፍ ታሪክ የላትምና ዛሬ አመራሮችና ተጠባባቂ ሃይሎች ይህን ታሪክ ለማስቀጠል ወደ ግንባር ተሸኝተዋል ብለዋል፡፡
በቀጣይም በተመሳሳይ እስከ ግንባር የሚዘምቱ አመራሮች ዝግጅት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
በእናቶች ከተደረገው ድጋፍ በተጨማሪም÷ ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ዞኑ በገንዘብ 7 ሚሊየን፣ በዓይነት 6 ነጥብ 9 ሚሊን ብር የሚገመት ድጋፍ ተደርጓል፡፡
በጥላሁን ሁሴን
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.