Fana: At a Speed of Life!

አንዳንድ ሃገራት ኢትዮጵያን ለማዳከም በታቀደ መልኩ እየሰሩ ነው – የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አንዳንድ ሀገራት ኢትዮጵያን በሁሉም ዘርፍ ለማዳከም በታቀደ መልኩ ጫና እያሳደሩ ነው ሲል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡
ሀገራቱ በተጠና መልኩ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ዲፕሎማሲያዊ ጫና እያሳደሩ መሆኑን ነው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ያስታወቁት፡፡
ሚኒስትሩ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሰጡት ማብራሪያ÷ የእነዚሁ ሀገራት ዓላማ ማስፈፀሚያ በሆኑት በ ሲ ኤን ኤን፣ ቢ ቢ ሲ፣ ሮይተርስ እና ኤ ፒ ብዙኃን መገናኛዎች የሚወጡት የተዛቡ ዘገባዎች የሀገርን ህልውና ለመጉዳት ታቅዶ የሚደረግ ዘመቻ አካል መሆናቸውን ህዝቡ ሊገነዘብ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ሕዝብ ባለው ጠንካራ አብሮነትና ለሀገሩ ሉዓላዊነት ያለው አቋም ጽኑ በመሆኑ÷ በተለያየ መንገድ በኢትዮጵያ ላይ እየተሰነዘረ የሚገኘው ጫና ይከሽፋልም ነው ያሉት፡፡
በሌላ በኩል በኤርትራ መንግሥት እና በአንዳንድ አመራሮች ላይ በአሜሪካ መንግሥት የተጣለው ማዕቀብ አግባብ እንዳልሆነና ማእቀቡ አጥቂውን ትቶ ተጠቂው ላይ በትር ማሳረፍ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ከሕወሓት አሸባሪ ቡድን የተሰነዘረበትን ጥቃት ለመመከትና የሀገሩን ሉዓላዊነት ለማስከበር በተገደደው የኤርትራ መንግሥት ላይ ማዕቀብ መጣል ለቀጣናው ሰላም እንደማይበጅ የኢትዮጵያ መንግሥት ይገነዘባልም ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያም ሆነ በቀጣናው ለሰላም ጠንቅ የሆነውን የሕወሓት አሸባሪ ቡድን ለመመከት በመላ ሀገሪቱ የተጀመረዉ የአርበኝነት ንቅናቄ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ዶ/ር ለገሰ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን የተጋረጠባቸውን የህልውና አደጋ በተባበረ ክንዳቸው ቀልብሰው÷ ጠንካራ ኅብረ ብሔራዊ አንድነቷ የተረጋገጠ ኢትዮጵያን በጋራ ይገነባሉም ብለዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.