Fana: At a Speed of Life!

የባእከር ጊዜያዊ የፖሊስ ማሰልጠኛ ለ9ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ልዩ ኃይሎች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን የባእከር ጊዜያዊ የፖሊስ ማሰልጠኛ ለ9ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን የአማራ ልዩ ኃይል አባላት አስመርቋል።
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ እንደገለጹት÷ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል በአማራና በአፋር ክልሎች ወረራ በመፈጸም ንጹሐንን እየገደለ፣ እየደፈረ፣ እያፈናቀለና እየዘረፈ መሆኑን ጠቁመው÷ “የዛሬ የልዩ ኀይል ተመራቂዎች የአማራ ሕዝብ ለሕልውናው የማይደራደር መኾኑን ማሳያ ትኾናላችሁ ብለን እናምናለን” ብለዋል፡፡
ተመራቂ የልዩ ኃይል አባላት ባገኙት የወታደራዊ ሳይንስ ስልጠና ማንኛውንም ችግር በመቋቋም÷ በዓላማ በመጽናት ጠላትን መደምሰስ እንደሚጠብቅባቸው ርዕሠ መስተዳድሩ አሳስበዋል፡፡
የሚደረገው ትግል የመኖርና ያለመኖር በመሆኑ÷ የአማራ ሕዝብ በጠላት እየተጎሳቆለ፣ እየተገደለ፣ እየተደፈረና እየተዘረፈ በመኾኑ ጠላትን ለማጥፋት ጊዜ መውሰድ እንደማያስፈልግ ተናግረዋል።
ተመራቂዎች በዓላማ ጸንተው ከወገን ኃይል ጎን በመሰለፍ በሚደረገው አውደ ውጊያ ድል በማድረግ የአማራንና የኢትዮጵያን ሕዝብ ታሪክ ማደስ እንደሚገባ አሳስበዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.