Fana: At a Speed of Life!

የምዕራባውያን ሚዲያዎች ምንጊዜም የአፍሪካ ስጋቶች ናቸው -የቀድሞው የጋና ፕሬዚደንት

አዲስ አበባ፣ ህዳር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የምዕራባውያን ሚዲያዎች ለአፍሪካ አህጉር የምንጊዜም ስጋቶች መሆናቸውን የቀደሞዉ የጋና ፕሬዚደንት ጄሪ ጆን ሮውሊንግ በህይዎት በነበሩበት ዘመን መናገራቸውን የተለያዩ ሚዲያዎች እያስታወሱት ነው፡፡

ፕሬዚደንቱ ካንዲድ አፍሪከ በተባለዉ የቴሌቪዥን ጣቢያ ካደረጉት ቆይታ በተወሰደዉ ማስታዎሻ ምዕራባውያንና ሚደያዎቻቸው የአፍሪካን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ገፅታ በማዛባት ሲሰሩ መቆየታቸዉን ተናግረዋል፡፡

ምዕራባዉያን ሚዲያዎች በአፍሪካ መሪዎች እና በሚመሩት ህዝብ እርስ በእርስ ጥርጣሬ እንዲኖር በማድረግ የአፍሪካዉያንን መልካም ገፅታ ሲያጎድፉ መቆየታቸውን የፕሬዚደንቱ ንግግር ያስታውሳል፡፡

አፍሪካውያንን ይህን ተፅዕኖ በመረዳት ነቅተዉ አሀጉራቸዉን መመለከት እንደሚገባቸዉ ምክረ ሃሳባቸዉን የሰጡት የቀድሞዉ ፕሬዚደንት ጄን ጆን ሮሊንግ ÷ ምዕራባዉያን ሚዲያዎች የሞራል ልዕልናም ሆነ ስነ ምግባር እንደሌላቸዉ ጠቁመዋል ነበር፡፡

ሉላዊነት የአለም ሁሉን አቀፍ ትስስርን የሚያጠናክር ቢሆንም ለአፍሪካዉያን ያላቸዉ እይታ የተዛባ ከሆነ እና የግል ፍላጎታቸውን የሚያስቀድሙ ከሆነ ጉዳቱ ከፍተኛ መሆኑንም ገለፀዋል፡፡

ለዚህም አፍሪካዉያን ከተኙበት ሊነቁ እንደሚገባም ነው በወቅቱ ያሳሰቡት፡፡

አፍሪካዉያን በምዕራባዉያን ሚዲያዎች ሁሉም ሙሰኞች፣ ሁሉም አምባ ገነን መሪዎች፣ በኢኮኖሚ ደካማ እና የመልካም አስተዳደር ችግር ያለባቸዉ ተደርገዉ ይወሰዳሉ ፤ ስለሆነም አፍሪካውያን ሰላምና እድገት የሚፈልጉ ከሆኑ ተፅዕኖዉን በአንድነት መመከት ይገባቸዋል ብለዋል ፕሬዚደንቱ፡፡

ከቅኝ ግዛት ነፃ ብንወጣም ምዕራባውያን አሁንም በሚዲያዎቻቸዉ ቅኝ ሊገዙን እየሞከሩ ነው ያሉት ፕሬዚደንቱ ÷ ያኔ ቅኝ ሲገዙን ግልፅ ጠላቶቻችን ነበሩ ፤ አሁን ግን የቅኝ ግዛት ቀንበራቸውን በስዉር ነዉ የሚያከናውኑት የሚለው ንግግራቸው አሁንም ድረስ በርካቶች እየተቀባበሉት ያደምጡታል።

በሚኪያስ አየለ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.