Fana: At a Speed of Life!

የመዲናዋ አስተዳደር በአፋር ግንባር ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው ሰንጋዎችን አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስስተዳድር በአፋር ግንባር የህወሀት ወራሪ ሀይልን በመፋለም ላይ ላሉ ለሀገር መከላከያ ሰራዊትና ልዩ ሃይል ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው ሰንጋዎችን ድጋፍ አደረገ።

የአስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ ሰመራ ከተማ ተገኝተው ድጋፍን ለአፋር ክልል ርዕሰ መአስተዳድርና ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አመራሮች አስረክበዋል።

ከንቲባ አዳነች አበቤ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት፥ ህወሃት በአፋርና አማራ አካባቢዎች የከፈተብንን የግፍ ወረራ ለመቀልበስ መከላከያና ልዩ ሃይሎች እያደረጉ ባለው ከፍተኛ ርብርብ ድል እየተመገበ ይገኛል።

የአፋር ህዝብ ከመከላከያ ሰራዊትና ልዩ ሀይል ጋር በመሆን ወራሪው ሀይል የሀገሪቱን የወጪና ገቢ ንግድ መስመር በመቆጣጠር ሀገር ለማፍረስ የወጠነውን ውኩይ ዐላማ በማክሸፍ ከፍተኛ ጀብድ መፈጸሙን ከንቲባዋ ተናግረዋል።

ለተመዘገበው ጀብድ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድርና ህዝብ ከፍተኛ ኩራት የተሰማቸው መሆኑን ገልጸው፥ የከተማ አስተዳድሩ ለሠራዊቱና ልዩ ሀይል ያለውን አጋርነት ለመግለጽ ከ10 ሚሊዮን በላይ ግምት ያላቸው 120 ሰንጋዎች ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል ።

አስተዳደሩ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ማስታወቃቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው ።

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ በበኩላቸው፥ “አሸባሪው ህወሃትና ከጀርባው የተሰለፉ የውጭ ሃይሎች ኢትዮጵያን ለማፍረስ የወጠኑት ሴራ በህዝቦቿ የተባባረ ክንድ እየተመከተ ይገኛል” ብለዋል።

“ከመከላከያ ሰራዊትና ልዩ ሃይል በተጨማሪ ህዝቡ አካባቢውን በመጠበቅና ጠላትን መፈናፈኛ በማሳጣት ትልቅ ገድል እየፈጸመ ነው” ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።

ለህይወት ሳይሰስት ለሀገርና ለህዝብ ደህንነት እየተዋደቀ ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊትና የክልሎች ጸጥታ መዋቅር ህዝቡ እየሰጠ ያለው ደጀንነትም ለድሉ መፍጠን የጎላ ሚና እንዳለው ነው ያመለከቱት።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ላደረገው ድጋፋ በክልሉ፣ በሀገር መከላከያና ልዩ ሃይል ስም አቶ አወል አመስገነዋል።

የሀገር መከላከያ ሠራዊትን በመወከል ድጋፉን የተረከቡት ኮሎኔል እሸቴ በሪሁን በበኩላቸው፤ ህዝቡ ለመከላከያ ሠራዊት እያደረገ ያለው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ የሚደነቅና የሚያኮራ መሆኑን ተናግረዋል።

ሰራዊቱ አሸባሪው ህወሃት በሀገር ላይ የፈጸመውን ክህደትና የግፍ ወረራ በአጭር ጊዜ በመቀልበስ የወራሪውን ግብአተ መሬት ለመፈጸም በቁርጠኝነት እየተፋለመ መሆኑንም ገልጸዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.