Fana: At a Speed of Life!

የሽብርተኞችን ጥቃት ለመከላከል በምንችለው ሁሉ ከመንግስት ጎን ነን – የሀገር ሽማግሌዎች

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 05፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሽብርተኞችን ጥቃት ለመከላከል በሚችሉት ሁሉ ከመንግስት ጎን በመሆን የድርሻቸውን እንደሚወጡ የጉጂ ዞን የሀገር ሽማግሌዎች ገለጹ፡፡

ከዞኑ ሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ 200 የሀገር ሽማግሌዎች ትናንት በነገሌ ከተማ የሰላምና የልማትን ኮንፈረንስ ተካሂዷል፡፡

የአገር ሽማግሌዎቹ “አገራችን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን እየተጋፈጠች በምትገኝበት በዚህ ጊዜ እኛም ከመንግስት ጎን ሆነን የድርሻችን ማበርከት ግዴታችን ነው” ብለዋል ።

ከአገር ሽማግሌዎቹ መካከል የነገሌ ከተማ ነዋሪ አቶ ኢያ ዋሪዎ “ሀገር ለማፍረው የተነሱ ጠላቶችን ለመፋለም እየተካሄደ ካለው የህልውና ዘመቻ በተጓዳኝ የሽብር ቡድኑ ህዝብን እንዲዘርፍ ሀገር እንዲያፈርስና በንጹሃን ላይ ጥቃት እንዲያደርስ የሚተባበሩ የውስጥ ባንዳዎችን ማጥራት እንደሚገባ አመልክተዋል።

ሌላው የከተማው ነዋሪ ወይዘሮ ፋጤ ዱባ “ሽብርተኛው ሸኔ ከዞኑ ጉሚ ኤልደሎ፣ ሊበን፣ ጎሮዶላና ሰባቦሩ ወረዳዎች የመንግስት ደጋፊ ናችሁ በሚል ንጹሃንን ማፈናቀሉን ቀጥሎበታል” ብለዋል፡፡

“በውስጥ አሸባሪዎችና በውጭ ጫናና ተጽእኖ ሳንረበሽ ሀገራችንንና አካባቢያችንን ነቅተን የመጠበቅ አቅምም ብቃቱም አለን” ያሉት ደግሞ አቶ መሀመድ በቸሎ ናቸው።

የኦሮሞ ህዝብ ያሳለፈውን ግፍና መከራ ረስቶ ዳግም በባርነት ለመኖር በሽብርተኛች ህወሀትና ሸኔ እንደማይመራ ገልጸዋል።

ኮንፈረንሱን የመሩት የኦሮሚያ ክልል ከተማ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጉዮ ገልገሎ “መንግስት ሀገር ለማፍረስ በሚሰሩ የውስጥና የውጭም የጥፋት ሃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የኦሮሞ ህዝብ ከሌላው ወንድም የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመሆን በህይወት መስዋእትነት ያገኘውን መልካም አጋጣሚ በሽብርተኞች ፕሮፓጋንዳ ተታሎ ነጻነቱን አሳልፎ እንደማይሰጥ በአጽንኦት ገልጸዋል ።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.