Fana: At a Speed of Life!

የህልውና አደጋውን መቀልበስ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 05፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደብረ ብርሃን ከተማ የሽብር ቡድኖቹ ህወሓት እና ሼኔን ሀገር የማፍረስ ሴራ መቀልበስ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከንግዱ ማህበረሰብ አባላት ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡
 
በውይይት መድረኩ የከተማዋ ተቀዳማ ከንቲባ አቶ ደስታ አንዳርጌን ጨምሮ የተለያዩ የሥራ ሃላፊዎችና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ተሳትፈዋል፡፡
 
ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ደስታ አንዳርጌ÷የንግዱ ማህበረሰብ የሽብር ቡድኖችን ሀገር የማፍረስ ሴራ ለማክሸፍ ሃብት ከማሰባሰብ ያለፈ አስተዋጽኦ ማበርከት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡
 
የገጠመን የህልውና አደጋ እንደ ህዝብ የሁላችንንም ሃላፊነት የሚጠይቅ ነው ያሉት ከንቲባው÷የከተማዋ የንግድ ማህበረሰብ ለህልውና ዘመቻው የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡
 
የከተማዋ የንግድ ማህበረሰብ አባላት በበኩላቸው÷ጦርነቱ ከፍተኛ የህዝብ ደጀንነት የሚያስፈልገው በመሆኑ አስፈላጊውን ሁሉ መስዋዕትነትለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
 
በኤልያስ ሹምዬ
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.