Fana: At a Speed of Life!

የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ነዋሪዎች ለተፈናቃዮች 5 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ነዋሪዎች ለተፈናቃዮች በአልማ አስተባባሪነት ያሰባሰቡትን 5 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የአይነት ድጋፍ አድርገዋል።
 
ድጋፉ ከአማራ ክልል በጦርነት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን ከተማ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ዜጎች ነው የተደረገው።
 
ድጋፉን በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 7 ብልጽግና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሚዲያ ሃላፊና የአልማ ኮሚቴ አስተባባሪ አቶ ሚኪያስ አውቀነው በስፍራው ተገኝተው አስረክበዋል።
 
የአይነትና ምግብ ድጋፉን የተረከቡት የሰሜን ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ወልደ አማኑኤል÷ የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ነዋሪዎች ለተፈናቃይ ወገኖች ለደረጉት ድጋፍ ምስጋናአቅርበዋል።
 
የትህነግ ሽብር ቡድን በህዝባችን ላይ እየፈጸመ ባለው ወረራ ወገኖቻችን እየተፈናቀሉ ነው ያሉት አቶ ሲሳይ ÷ ጁንታውን በጋራ ለመደምሰስ እየተደረገ ካለው ርብርብ ጎን ለጎን የተፈናቀሉ ወገኖችን በጋራ ለመርዳት እየተደረገ ያለው አጋርነት በጋራ መቆማችንን ያሳያል ብለዋል።
 
ተፈናቃዮችን ለመደገፍ እየተደረገ ያለው ርብርብ ሰፊ ቢሆንም ከችግሩ ስፋት አንጻር በቂ ባለመሆኑ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል።
 
በግርማ ነሲቡ
 
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.