Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ለህንድ ኤስ-400 የተሰኘውን የሚሳኤል መቃወሚያ መላክ ጀመረች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ኤስ-400 የተሰኘውን የሚሳኤል መቃወሚያ ስርዓት ለህንድ መላክ መጀመሯን አስታውቃለች፡፡
 
ኒው ዴልሂ ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ ከአሜሪካ ሊጣልባት የሚችልን ማዕቀብ ወደ ጎን በመተው ነው የሚሳኤል መቃወሚ ስርዓቱን ከሞስኮ ማስላክ የጀመረችው።
 
ህንድ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2018 ኤስ-400 የተሰኘውን የሚሳኤል መቃወሚያ ስርዓት ከሩሲያ ለመግዛት መስማማቷ ይታወሳል።
 
በዚህ መሰረትም ህንድ ከሩሲያ 5 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ዋጋ የሚያወጡ አምስት ኤስ-400 የሚሳኤል መቃወሚያዎችን ለመግዛት ውል ፈፅማለች።
 
ይህን ተከትሎም አሜሪካ ኒው ዴልሂ ከሞስኮ የሚሳኤል መቃወሚ ስርዓት ለመግዛት የፈጸመችውን ስምምነት እንድትሰርዝ ስታስጠነቅቅ ቆይታለች።
 
አሁን ላይም ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ ህንድ ከአሜሪካ ሊጣልባት የሚችልን ማዕቀብ ወደ ጎን በመተው የሚሳኤል መቃወሚ ስርዓቱን ከሩሲያ ማስላክ መጀመሯ ን አናዶሉ ዘግቧል።
 
ኤስ-400 ከመሬት ወደ አየር ተወንጫፊ የሚሳኤል መቃወሚያ ስርዓት የህንድን ወታደራዊ አቅም ይበልጥ ማጠናከር ያስችላል ተብሎ ታምኖበታል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.