Fana: At a Speed of Life!

ለአሸባሪው ህወሓት ድጋፍ ሊውል የነበረ 37 ሺህ ዶላርና የጦር መሳሪያ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ለአሸባሪው ህወሓት ድጋፍ ሊውል የነበረ 37 ሺህ የአሜሪካ ዶላር፣ በርካታ ገንዘብና የጦር መሳሪያዎች መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡
 
ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎቹ እና ገንዘቡ የተያዘው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ወንድይራድ ትምህርት ቤት አካባቢ ፖሊስ ሕብረተሰቡ የሰጠውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ባከናወነው ፍተሻ ነው ተብሏል፡፡
 
የኮተቤ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ሃላፊ ኮማንደር በየነ ዱሬሳ÷ ህብረተሰቡ የሰጠውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት በተደረገ ፍተሻ ግለሰቡ በብርበራ እንዳይገኝበት በማሰብ 37 ሺሕ የአሜሪካ ዶላር፣ 52 ሺሕ ብር እና የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦችን በፌስታል ጠቅልሎ ግቢው ውስጥ ደብቆ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡
 
ሀገርን ለማዳን የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ በማድረግ የፖሊስ አመራርና አባላቱ በቅንጅት የህግ ማስከበር ስራ በመስራታቸው ጥሩ ውጤቶች እንደተገኙ መግለጻቸውንም ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.