Fana: At a Speed of Life!

ለሽብር ዓላማ ማስፈፀሚያ ሊውሉ የነበሩ ቁሳቁሶች በቁጥጥር ስር ዋሉ

 

 

አዲስ አበባ፣ህዳር 5፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ለአሸባሪዎቹ የህውሃትና የሸኔ ቡድኖች እኩይ ዓላማ ማስፈፀሚያ ሊውሉ የነበሩ በርካታ ሲም ካርዶች፣ ሀሰተኛ የመሳሪያ ፍቃድና የሽጉጥ ጥይት ከ2 ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።

በህብረተሰብ ጥቆማና ፖሊስ ባከናወነዉ የኦፕሬሽን ሥራ ከ2 ተጠርጣሪዎች ጋር ነው በቁጥጥር ሥር የዋሉት።

አሸባሪዎቹ የህወሓትና የሸኔ ቡድኖች ሀገርን ለማፈራረስ እኩይ አላማ አንግበውና መድናችን አዲስ አበባን የጦርነት አውድማ ለማድረግ ተላላኪ ባንዳዎችን አሰማርተው እየተንቀሳቀሱ ቢገኙም ህዝቡና የፀጥታ አካላቱ ተቀናጅተው በሰሩት ጠንካራ ሥራ ሴራቸው እየከሸፈ ይገኛል።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው ሸራ ተራ የካቲት 23 ት/ቤት ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ሲሆን ለሽብር ቡድኖቹ እኩይ ዓላማ ማስፈፀሚያ የሚውሉ 2 መቶ 76 ሲም ካርዶችና ሀሰተኛ የጦር መሳሪያ ፍቃዶች እንዲሁም የሽጉጥ ጥይቶች በህብረተሰቡ ጥቆማ የኢንተለጀንስና የክትትል ቡድኑ ባከናወነው የኦፕሬሽን ስራ ነው።

ተጠርጣሪዎቹ በግለሰብ መኖሪያ ቤትና ይዘው ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ት/አደጋ ምርመራ ምክትል ዳይሬክተር መረጃው መገኘቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

የአሸባሪ ቡድኖቹን እኩይ ዓላማዎች ማክሸፍና መደምሰስ የሚቻለው በተባበረ የህዝብ ተሳትፎ መሆኑን የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ፥ ሰላም ወዳድ የሆነው ህዝባችን የአሽብር ቡድኖቹን ተላላኪ ባንዳዎችን አጋልጦ በመስጠት እንደ ከዚህ ቀደሙ ትብብሩን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጥሪውን አቅርቧል።

ምንጭ :- የአዲስ አበባ ፖሊስ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.