Fana: At a Speed of Life!

“የውጭ ጫናው ኢትዮጵያ ጠንካራ ከሆነች አፍሪካም ትጠነክራለች ከሚል ስጋት የመነጨ ነው” – አባዱላ ገመዳ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ላይ እየመጣ ያለው የውጭ ጫና ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን አስጠብቃ ጠንክራ ከወጣች አፍሪካም ትጠነክራለች ከሚል ስጋት የመነጨ መሆኑን አቶ አባዱላ ገመዳ ገለጹ፡፡

አቶ አባዱላ ገመዳ ÷ ኢትዮጵያ ላይ የውጭ ጫና እየበረታ የመጣው መንግሥት በሁሉም መንገድ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚያስከብርና የሕዝብን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፎ እንደማይሰጥ እና የትኛውንም የእጅ ጥምዘዛ እንደማይቀበል በመግለጹ ነው ብለዋል፡፡

የውጭ ሃይሎች ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን አስጠብቃ ጠንክራ ከወጣች አፍሪካም ትጠነክራለች የሚል ስጋት ስላላቸው ጫና ለማሳደር እየተረባረቡ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡

እንደ አቶ አባዱላ ገለጻ ÷ ያለፉት መንግሥታትም አባይን የማልማት ፍላጎቱ ቢኖራቸውም አቅም ስላልነበረንና የትኛውም አገር ብድር እንዳያበድርና እንዳይደግፍ በመደረጉ በእኛ ውሃ ሌሎች እየተጠቀሙ ኢትዮጵያዊያን ያለንን የተፈጥሮ ሐብት ሳንጠቀም በድህነትና በጨለማ ውስጥ እንድንኖር ተደርጓል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.