Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያውያን ከምንጊዜውም በላይ ለአገራቸው በአንድነት መቆም ይገባቸዋል – አምባሳደር ደሚቱ ሃምቢሳ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጣልያን እና ግሪክ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም እያዘጋጁ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያውያኑ እና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ለመከላከያ ሰራዊት እና ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ለማካሄድ በተጠናከረ ሁኔታ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

በጣልያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሣ በስብሰባው በመገኘት ባስተላለፉት መልዕክት ስለተከናወኑ ሥራዎች ምስጋናቸውን ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከምንጊዜውም በላይ ከሀገራችው ጎን በአንድነት መቆም እንደሚገባቸው አጽንኦት ሰጥተው መግለጻቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.