Fana: At a Speed of Life!

የለገጣፎ ለገዳዲ የባጃጅ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች ለመከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር የባጃጅ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች በዘመቻ መልክ ለአገር መከላከያ ሠራዊት ደም ለገሱ።

የከተማው የትራንስፖርት ባለስልጣን ሃላፊ አቶ ተፈራ ደምሴ ÷ ከ233 የሚበልጡ የከተማዋ የባጃጅ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች በግዳጅ ላይ ለሚገኘው የአገር መከላከያ ሠራዊት ደም መለገሳቸውን ተናግረዋል።

የባጃጅ አሽከርካሪዎቹና ባለንብረቶች ደማችንና ገንዘባችን ከአገር አይበልጥም በማለት ስራቸውን አቁመው ደም መለገሳቸውን ገልጸዋል።

እንደ ባጃጅ ማህበር ከ70 ሺህ ብር በላይ፥ በግል ደግሞ ከ500 እስከ 1 ሺህ ብር ለአገር መከላከያ ሠራዊት የገንዘብ ድጋፍ አድርገናል ማለታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.