Fana: At a Speed of Life!

አፍሪካውያን ነጻነታቸውን ሁልጊዜም ሊጠብቁት ይገባል – በኢትዮጵያ የአንጎላ አምባሳደር

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካውያን የአገራቸውን ነፃነትና ሉዓላዊነት በየዓመቱ ቀን እየጠበቁ የሚያከብሩት ብቻ ሳይሆን ሁሌም የሚጠብቁት እና ዘብ የሚቆሙለት ሊሆን እንደሚገባ በኢትዮጵያ የአንጎላ አምባሳደር ፍራንሲስ ጆዜ ዳ ክሩዝ አሳሰቡ፡፡

አንጎላም ሆነች ሌሎች የአፍሪካ አገራት ከቅኝ ገዢዎቻቸው ነፃ ለመውጣት ብርቱ ተጋድሎ በማድረግ ነፃ ከወጡ በኋላ ቀኑን ከማክበር ባለፈ ዋጋ የከፈሉለትን ነፃነት ሲያስጠብቁ አይታይም፤ ይህም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የውጭ ኃይሎች መጠቀሚያ እያደረጋቸው ይገኛል ብለዋል አምባሳደሩ፡፡

“እኛ አንጎላውያን ምንም እንኳን ከቅኝ ግዛት ብንላቀቅም ነፃ በወጣን ማግስት የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ መግባታችን ብዙ ዋጋ አስከፍሎናል” ብለዋል አምባሳደሩ።

ለዚህ ደግሞ በዋናነት የውጭ አገራት ጣልቃ ገብነት ችግሩ የከፋ እንዲሆንና ዓመታትን እንዲሻገር አድርጎት እንደቆየ መናገራቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.