Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲና የራሽያ ዩናይትድ ፓርቲ ግንኙነታቸው በሚጠናከርበት ዙሪያ መከሩ

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አደም ፋራህ እና በኢትዮጵያ የሩሲያ ፌዴሬሽን አምባሳደር ኢቨጌኒ ቴረኺን የብልጽግና ፓርቲና የሩሲያ ዩናይትድ ፓርቲን ግንኙነት በሚጠናከርበት ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በፓርቲዎቹ መካከል የተፈረመውን የመግባቢያ ሰነድ መሰረት ባደረገ መልኩ የፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነቱን ተግባራዊ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

ፓርቲዎች በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ሁለንተናዊ ግንኙነት በሚያጠናክር መልኩም ለመስራት ተግባብተዋል፡፡
አቶ አደም ፋራህ በውይይቱ እንዳነሱት የኢትዮጵያና የሩሲያ ፊዴሬሽን ከመቶ ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ግንኙነት እንዳላቸው አንስተው የሩሲያ ፌዴሬሽን ምንጊዜም ለኢትዮጵያ ለሚያደርገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የሩሲያው አምባሳደር በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያና ሩሲያ በተለያዩ መስክ የጀመሩትን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር የፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነቱ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም አምባሳደሩ ከሞስኮ የተላከ መልዕክት ለብልጽግና ዋና ጽህፈት ቤት ሃላፊው ማስረተላለፋቸውን ከብልፅግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.