Fana: At a Speed of Life!

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሀገርን ህልውና ለመታደግ ያለመ በመሆኑ ሁሉም ሀላፊነቱን እንዲወጣ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የሰራዊት አባላትና በምስራቅ ወለጋ ዞን የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ አባላት እንደ ሀገር በተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዝርዝር አፈፃፀም እና የአስፈፃሚ አካላት ሚና ላይ ተወያዩ፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አሸባሪው ህወሓትና ሸኔ የሀገርን ህልውና አደጋ ላይ ለመጣል የደቀኑትን ስጋት የመከላከል ዓላማ አለው ሲሉ የምዕራብ ዕዝ መሀንዲስ መምሪያ ሃላፊ ኮ/ል ግርማ ወንዳፍራሽ ተናግረዋል፡፡
የምዕራብ ዕዝ ፍትህ ቡድን ሃላፊ ሌ/ኮ ንጉሴ አበባው በበኩላቸው÷ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተቀመጡ ዝርዝር ጉዳዮች የአሸባሪ ቡድኖችን እኩይ አላማ በማክሸፍ የሀገርን ህልውና መታደግ በመሆኑ ለተግባራዊነቱ ሁሉም ሀላፊነቱን በአግባቡ ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ለአሸባሪ ቡድኑ የቁስም ሆነ የሞራል ድጋፍ ያደርጋሉ ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦችም ይሁን ድርጅቶች ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መበርበርና ፍተሻ ማድረግ አዋጁ እንደሚፈቅድም ተገልጿል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንደ ሃገር ሰላምን ለማረጋገጥ የወጣ ስለሆነ÷ በዚህም የጋራ ግልፀኝነት በመፍጠራቸው የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት ስለ መዘጋጀታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.