Fana: At a Speed of Life!

የኮንትሮባንድ ንግድን ለመከላከል በትብብር እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮንትሮባንድ ንግድን ለመከላከል ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን የጉሙሩክ ኮሚሽን አሶሳ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
 
በመርኃ ግብሩ የጉሙሩክ ኮሚሽን አሶሳ ቅርጫፍ ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ሙስጠፋ አዜን እንዳሉት የገቢና ወጪ ኮንትሮባንድን ለመከላከል የግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች እየተሰራ ነው።
 
ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ከአራት ተቋማት ጋር በጋራ መስራት የሚያስችል መግባቢያ ሰነድ የተፈራረመ ሲሆን የጋራ መግባቢያ ሰነዱን የፈረሙ ተቋማትም ህገ-ወጥነትን ለመከላከል ድርሻቸው የጎላ መሆኑንም ስራ አስኪያጁ ጠቁመዋል።
 
ከጠረፍ ንግድ ጋር ተያይዞ በማህበረሰቡ ዘንድ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የክልሉ መንግስት ከሚመለከታቸው የፌደራል ተቋማት ጋር ሰፊ ስራ መስራት ይጠበቅበታልም ብለዋል።
 
የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ አቶ ለሜሳ ዋወዬ በበኩላቸው የኮንትሮባንድ ንግድን መከላከል ካልተቻለ በአገር ምጣኔ ሀብት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚኖረው ጠቁመዋል።
 
በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ አመራሮችና ባለሙያዎች ሰፊ ስራ መስራት ይጠበቅባቸዋልም ነው ያሉት።
 
የክልሉ ማህበረሰብም በጠረፍ ንግድ ተጠቃሚ እንዲሆን በዘርፉ የሚስተዋሉ ክፍተቶች እንዲታረሙ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት ይሰራል ማለታቸውን ከክልሉ መገናኛ ብዙሃን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
 
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.