Fana: At a Speed of Life!

ተመድ ለኢትዮጵያ የ40 ሚሊየን ዶላር እርዳታ ፈቀደ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለኢትዮጵያ ለሰብአዊ ድጋፍና አስቸኳይ ጊዜ እርዳታ የሚውል የ40 ሚሊየን ዶላር መፍቀዱን አስታውቋል።
 
የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ምክትል ፀሃፊና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፍትስ፥ ገንዘቡ አሁን ላይ ባለው ግጭት ተጎጂ ለሆኑ ዜጎች የሚውል ነው ብለዋል።
 
ከዚህ ባለፈም በደቡብ የሀገሪቱ ክፍል ለተከሰተው ድርቅ አስቀድሞ ምላሽ ለመስጠት ይውላለም ነው የተባለው።
 
ከተለቀቀው ገንዘብ ውስጥ 25 ሚሊየን ዶላሩ ከተባበሩት መንግስታት ማዕከላዊ የአደጋ ጊዜ ምላሽ ፈንድ የተገኘ ሲሆን፥ ቀሪው በኢትዮጵያ ከሚገኘው የሰብአዊ እርዳታ ፈንድ ነው።
 
ገንዘቡ በተለይም በትግራይ፣ በአማራ እና አፋር ክልል የሚንቀሳቀሱ ረጂ ድርጅቶችን በማገዝ የሚደረገውን የህይወት አድን ስራ ለማገዝ እንደሚውል የድርጅቱ መረጃ ያመላክታል።
 
በተጨማሪም በደቡባዊ ሶማሌ እና ኦሮሚያ ክልሎች በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች ለቀንድ ከብቶችና ለነዋሪዎች የንጹህ መጠጥ ውሃ ለማቅረብና ውሃ ወለድ በሽታዎችን ለመከላከል እንደሚውልም ተገልጿል።
 
በሚኪያስ አየለ
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.