Fana: At a Speed of Life!

የውጭ ዜጎች ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ ቢወተወቱም ለመውጣት የሚጋፋ ሰው አይታይም – አምባሳደር ፍጹም

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካና አጋሮቿ የሚደረገውን ውትወታና ያልተገባ መረጃ ተከትሎ የውጭ አገራት ዜጎች እንዲወጡ ቢጠየቅም አዲስ አበባን ለቆ ለመውጣት የሚጋፋ ሰው አለመታየቱን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፍጹም አረጋ ገለጹ።

አምባሳደሩ ÷በዋሽንግተን ከስፑትኒክ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳስረዱት፣ አዲስ አበባ እንደወትሮው አስተማማኝ ሠላም ያላት፣ ጸጥታዋም የተጠበቀና ኑሮም በተለመደው መልኩ የቀጠለ በመሆኑ በአስቸኳይ ለቃችሁ ውጡ የሚለው ቅስቀሳ አልሰራም ብለዋል።

በአዲስ አበባ ያሉ የውጭ አገራት ዜጎች ከተማዋን ለቀው የሚወጡበት አሳማኝ ምክንያት አለመኖሩንም አምባሳደሩ አስረድተዋል።

አምባሳደሩ በሌሎች አገራት ችግሮች ሲፈጠሩ ይታይ እንደነበረው ዓይነት እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ እንደሌለ ገልጸው፣ የተለያዩ አገራት ዜጎች በአስቸኳይ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ ላለፉት ሁለት ሳምንታት የተካሄደው ያልተቋረጠ ውትወታ አለመሳካቱን ተናግረዋል።

አምባሳደሩ የአሜሪካ መንግስት የውጭ ዜጎች ኢትዮጵያን እንዲለቁ ላስተላለፈው ቅስቀሳ በርካታ የአውሮፕላን ጉዞ ትኬቶችን ቢያዘጋጅም የውጭ ዜጎች የታሰበውን ያህል ለቀው እየወጡ አለመሆኑን ጠቁመው፥ 120 ሚሊየን ህዝብና ሰፊ መልክአ ምድራዊ ገጽታ ባላት ኢትዮጵያ ግጭቱ የተከሰተበት ቦታ ትንሽ መሆኑንም አንስተዋል።

ከተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ መንግስት በአዲስ አበባ ለሚገኙ የዲፕሎማሲው ማኅበረሰብ አባላት የደህንነት ዋስትና መስጠቱን ያስታወሱት አምባሳደር ፍጹም፥ አንዳንድ አገራት ዜጎች ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ በመወትወት በሚፈጠረው ጫና ህወሓትን ለመርዳት ጥረት እያደረጉ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ ወደ ቀደመው ሰላሟ ሙሉ ለሙሉ እንደምትመለስም አምባሳደሩ ጨምረው መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.