Fana: At a Speed of Life!

ህወሓት አይደለም ኢትዮጵያን ትግራይን እንኳን የማስተዳደር ዕድል የለውም – የፋኖ ብርጌድ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው እና ወራሪው የህወሓት ቡድን አይደለም ኢትዮጵያን ይዞ ሊያስተዳድር በቀጣይ ትግራይን እንኳን የማስተዳደር ዕድል የለውም ሲሉ የፋኖ ብርጌድ መሪ ሻለቃ ሰፈር መለሰ ተናገሩ፡፡
ፋኖ ከወትሮው በተለየ በመንግስት ፈቃድና ድጋፍ በሻለቃና በብርጌድ መደራጀቱን ሻለቃ ሰፈር መለስ ገልጸዋል፡፡
የፋኖ አደረጃጀት በዚህ መንገድ መዋቀሩም የአማራን ህዝባዊ ኃይል የሚያጠናክር ከመሆኑም በተጨማሪ በፋኖ ስም የሚነግዱ አካላትን በማስቀረት ትክክለኛና የተደራጀ የህዝብ ሰራዊት እንዲኖር ያስችላል ብለዋል።
ይህ በሻለቃና በብርጌድ የተደራጀው የፋኖ ኃይል ከመከላከያ ሰራዊቱ፣ ከአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ጋር በመቀናጀት ጠላትን እየተፋለመ እንደሚገኝም ነው አዛዡ የተናገሩት፡፡
የብርጌዱ መሪ በግንባሩ የሚገኘው አጠቃላይ ሰራዊት እርስ በርሱ ተቀናጅቶና ተናቦ ጠላትን ለመቅበር እየታገለ ነው ብለዋል፡፡
ፋኖ የራሱን ግንባር በመያዝ የጠላትን ምሽግ እየደረመሰ በአሸባሪው ቡድን ላይ ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ እንዲሁም የሞራል ኪሳራ እያደረሰ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ጠላት የተለያዩ ጠንካራ ምሽጎችን በመስራት በተደጋጋሚ ጥቃት ለመሰንዘር ጥረት ቢያደርግም÷ የፋኖ ኃይል ፀረ ማጥቃት በማድረግ ሁለት የጠላት ምሽጎችን በመስበር ጀብዱ ፈፅሟል፣ በርካታ የጠላትን ኃይል በመደምሰስ ትጥቆችን ማርኳል ብለዋል፡፡
የህልውና ትግላችን ጠላትን ማሸነፍ እና ከወረራቸው አካባቢዎች ማስወጣት ብቻ ሳይሆን÷ ዳግም ለኢትዮጵያ ስጋት በማይሆንበት ደረጃ እስከ መቅበር ድረስ ነው ማለታቸውን ከአማራ ብልጽናግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.