Fana: At a Speed of Life!

ምዕራባውያንና መገናኛ ብዙኃኖቻቸው ስለጦርነቱ መነሻ እውቅና መስጠት አይፈልጉም – ኢ/ር ግደይ ዘረዓጽዮን

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምዕራባውያንና ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃኖቻቸው ለሴራና ለሀሰት ፕሮፓጋንዳ በመቆማቸው ለጦርነቱ መነሻ ምክንያት እውቅና መስጠት እንደማይ ፈልጉ የህወሓት መስራችና አንጋፋ ፖለቲከኛ ኢንጂነር ግደይ ዘረዓጽዮን ገለጹ።

ኢንጂነር ግደይ ዘረዓጽዮን ለኢፕድ እንደገለጹት ÷ ምዕራባውያንና ሚዲያዎቻቸው መንግሥት በትግራይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደፈጸመና የትግራይ ህዝብ ላይ በደል እንዳደረሰ አስመስለው ህዝባቸውን በሀሰት መረጃ አሳምነዋል።

እነዚህ አገራትና ዓለም አቀፉ መገናኛ ብዙኃን የጦርነቱ መነሻ ምክንያት ምን እንደነበር እውቅና መስጠት የማይፈልጉ ናቸው ብለዋል።

ሕወሓት ጦርነቱን እንደጀመረው ዓለም አቀፉን መገናኛ ብዙኃን ለማደናገር የተጠቀመበት ሂደት ፈጣን እንደነበር ኢንጂነር ግደይ ዘርዓጽዮን አስታውሰዋል።

ከእርሱ ጋር ግንኙነት የነበራቸውና ‘ተመራማሪ ነን’ የሚሉ፣ ታዋቂ ሰዎችንና በየአገራቱም ከመንግሥታት ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሰዎች ተጠቅሞ በአንድ ጊዜ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ማሰራጨቱን ገልጸዋል።

ይሁንና አሸባሪው ሕወሓት በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት አድርሶ ጦርነት መጀመሩን የሚያውቁ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን እውነታውን ከመዘገብ መቆጠባቸውን ጠቅሰዋል።

ጦርነቱ በተቀሰቀሰ ወቅት የአውሮፓ ህብረትም ሆነ የብሪታንያ ፓርላማ ትግራይ ላይ የተፈጸመ የዘር ማጥፋት ሂደት በማለት ተከራክረው ውሳኔ ከማሳለፍ ይልቅ የጦርነቱ መንስኤ ምን እንደነበርና ምን ሙከራዎች ተደርገው እንደነበር የሚሉ እውነታዎችን መግለጽ እንዳልፈለጉ ኢንጂነር ግደይ ተናግረዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.