Fana: At a Speed of Life!

የጤና ሚኒስቴርና የብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት አመራርና ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴርና የብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት አመራርና ሰራተኞች በግንባር ዋጋ እየከፈሉ ለሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ደም በለገሱበት ወቅት፥ አሁን ባለው አገራዊ ሁኔታ ደም የሚያስፈልጋቸው ወገኖች በርካታ መሆናቸውን አንስተዋል።
የተቋሙና የብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት አመራርና ሰራተኞችም በግንባር የአገር ህልውናን ለማስጠበቅ መስዋዕትነት እየከፈሉ ካሉ ወገኖች ጎን መሆናቸውን ለማሳየት የደም ልገሳ እና የቁሳቁስ ድጋፎች እያደረጉ ይገኛሉ።
ህብረተሰቡም አሁን ባለው ሃገራዊ ሁኔታ ያሳየውን የደም ልገሳ ስራ በማድነቅ ከዚህ በኋላም ባህል ሆኖ መቀጠል እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።
ሚኒስትሯ አያይዘውም በህልውና ዘመቻው የድንገተኛ አደጋ ምላሽ አሰጣጡን አስመልክቶም ገለጻ አድርገዋል።
በዚህም ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች አስቸኳይ ርዳታዎችን እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል።
ከዚህ ባለፈም ለህጻናት አልሚ ምግቦችና የተመጣጠኑ ምግቦችን የማድረሱ ስራም እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትሯ አንስተዋል።
የዛሬው የደም ልገሳና የቁሳቁስ ድጋፍም የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች ከጤናው ዘርፍ ባለፈም በዚህም ከጎናቸው መሆናቸውን ለማሳየት ነው ተብሏል።
የኢትዮጵያ ደምና ቲሹ ባንክ
በዙፋን ካሳሁን እና ሃይማኖት ኢያሱ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.