Fana: At a Speed of Life!

ዩኒቨርሲቲው የህልውና ዘመቻው በድል እስኪጠናቀቅ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የሚገመት የስንቅ ድጋፍ በታችጋይንት ለሚገኘው የወገን ጦር አስረክቧል፡፡
 
በዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ጉዳዮች ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር አቶ ገደፋው ሽፈራው ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት÷ ዩኒቨርሲቲው ከዚህ በፊት በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ለተፈናቀሉ ወገኖች እና ለፀጥታ ኃይሉ ድጋፍ ማድረጉን አንስተዋል፡፡
 
አሁንም ዩኒቨርሲቲው 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የሚገመት 200 ኩንታል የዳቦ ዱቄትና 2 ኩንታል የበርበሬ ዱቄት ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡
 
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ዲን ዶክተር ምንይችል ጌታው በተማሪዎች ጥያቄ ዩኒቨርሲቲው ተዘግቶ ሙሉ አቅሙን በህልውና ማስከበር ዘመቻው ላይ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡
 
ሌሎች ተቋማትም የኢትዮጵያን አፍራሽ ኀይል ለመደምሰስ መረባረብ አለባቸው ብለዋል፡፡
 
ድጋፉን የተረከቡት የደቡብ ጎንደር ዞን የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ አቶ አገኘሁ ካሳው ዩኒቨርሲቲው ኢትዮጵያን ከመፈራረስ እየታደገ ላለው የፀጥታ ኃይል ስንቅ በማቅረብ፣ ውድመት የደረሰባቸውን ወገኖች በመደገፍና መልሶ በማልማት እየሠራ ያለው ተግባር የሚበረታታ ነው ብለዋል፡፡
 
የህልውና ማስከበር ዘመቻው በድል እስኪጠናቀቅ ድረስ ሕዝቡ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ ማቅረባቸውንም አሚኮ ዘግቧል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.