Fana: At a Speed of Life!

በትምህርቱ ዘርፉ ተጨማሪ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ይገባል – ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በትምህርቱ ዘርፍ የሚደረገውን ኢንቨስትመንት ማሳደግ እንደሚገባ ገለጹ።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የዩኔስኮ ዋና ዳይሬክተር ኦድሪ አዙላይ ባዘጋጁት የዓለም አቀፉ የትምህርት ስብሰባ ላይ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።

ፕሬዚዳንቷ በበይነ መረብ አማካኝነት ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ እንዳነሱት ÷ በትምህርት ዘርፉ ላይ ተጨማሪ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ይገባል ብለዋል።

በተጨማሪም ፕሬዚዳንቷ እንደ ዓለም አቀፍ የትምህርት ኮሚሽን ሰብሳቢነታቸው በወደፊቱ የትምህርት ዘርፍ የመላው ሴቶችን በተለይም በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት ሰለባ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ተጠቃሚነት አኳያ ጥረት እንደሚያደርጉም ነው የገለጹት።

ፕሬዚዳንቷ የኮሚሽኑ አባላት ባለፉት ሁለት ዓመታት በተደረጉ 19 ስብሰባዎች ላሳዩት ቁርጠኝነት አመስግነዋል።

አያይዘውም የተመድ የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በሰዎች አዕምሮ ውስጥ ሰላምን የመገንባት ሃላፊነት አለበት ማለታቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ፕሬዚዳንቷ በንግግራቸው የሰላም ባህል እንዲዳብር እና ትምህርትን ለሰላም ማዋል በሚቻልበት አግባብ ላይ መስራት ይገባልም ብለዋል።

ትምህርትም ከዚህ አንጻር ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ጠቁመዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.