Fana: At a Speed of Life!

ፋይዘር ክትባት እድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሰዎች መስጠት ሊጀመር ነው

አዲስ አበባ፣ህዳር 7 ፣2014 (ኤፍቢሲ) የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ትናንት በአገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የኮቪድ19 ክትባት ዘመቻን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።
 
ሚኒስትሯ በመግለጫቸው ፋይዘር የተሰኘው ክትባት በአዲስ አበባ ከነገ ጀምሮ በክልል 65 ከተሞች ላይ ደግሞ ከሰኞ ጀምሮ እንደሚሰጥ ተናግረዋል።
 
በክትባት ዘመቻው ፋይዘርን ጨምሮ ከዚህ ቀደም ሲሰጡ የነበሩ ሶስቱም የክትባት አይነቶች በመንግስት ሁሉም የጤና ተቋምና ጊዜያዊ የክትባት መስጫ ማዕከላት ይሰጣል ብለዋል።
 
አሁን ባለው ሃገራዊ ሁኔታ ተፈናቅለው በመጠለያ ካምፕ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችም ቅድሚያ እንጸሚሰጣቸው ሚኒስትሯ ተናግረዋል።
 
አሁን ላይ 8 ሚሊየን ክትባት ዶዝ እንዳለ የተናገሩት ዶክትር ሊያ በቅርቡ 9 ነጥብ 6 ሚሊየን ክትባት ዶዝ እንደሚገባ ገልጸዋል።
እስካሁን 3 ነጥብ 7 ሚሊየን ሰዎች ክትባቱን መውሰዳቸውን ሚኒስትሯ አስታውቀዋል።
በሃይማኖት ኢያሱ

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.