Fana: At a Speed of Life!

የመዲናዋ ነዋሪዎች ለሕልውና ዘመቻው የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአገር ህልውና ላይ የተደቀነውን አንገብጋቢ የህልውና አደጋ በሁሉም ዘርፍ ርብርብ በማድረግ የህልውና ዘመቻ ግብረ ሃይል አቋቁሞ በአጭር ጊዜ የሚተገበር መርሃግብር መንደፉን የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታወቀ።
ምክር ቤቱ ዛሬ በሰጠውመግለጫ አባቶቻችን የአገርን ሉአላዊነት እና የህዝቧን አንድነት የህይወት መስዋዕትነት ከፍለው ያስረከቡንን አገር ለቀጣዩ ትውልድ ነጻ አድርጎ የማስረከብ ሃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባልም ብሏል።
የኢትዮጵያን ታላቅነት እና እድገት ከማይሹ የውጭ ሃይሎች ጋር ውል አልባ ጋብቻ ፈጽመው አገርን ለማፍረስ ሲታትሩ ለእኩይ ሴራቸው ተባባሪ ከሆኑ በስተቀር እጁን አጣጥፎ የሚመለከት አንድም ኢትዮጵያዊ ዜጋ የለም ነው ያለው ምክር ቤቱ።
አገራችንን ለመጠበቅ ሳንወድ ተገደን የገባንበትን ጦርነት በድል አጠናቀን የህዝባችንን ተስፋ ለማለምለምና የፈረሱ መሰረተ ልማቶችን መልሰን ለመገንባት እንድንችል የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለዚህ ጥሪ ምላሽ እንብዲሰጥም ጥሪውን አቅርቧል።
ዛሬ በአገር ላይ የገጠሙ ችግሮችን ለመፍታት በሚደረገው ጦርነት በሃሳብ በገንዘብ እና በፕሮፖጋንዳም የጋራ ምክር ቤቱ የበኩሉን እንደሚወጣም አስታውቋል።
በይስማው አደራው
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.