Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል የእንስሳት በሽታ ክትባት ዘመቻ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል በቀብሪ በያ ወረዳ በገብሪ እና በጊሎ ቀበሌዎች ድንበር ተሻጋሪ የእንስሳት በሽታ ክትባት ዘመቻ የፌደራልና የክልሉ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በይፋ ተጀመረ፡፡
ክትባቱ የሚሰጠው የከብትና የፍየል ሳንባ በሽታ፣ የደስታ መሰል የበጎችና የፍየሎች በሽታ በዓለም አቀፍ የእንስሳት ጤና ድርጅት የተለዩ ድንበር ዘለል የእንስሳት በሽታዎች መሆናቸውን የእንስሳት ሃብት ሚኒስትር ዲኤታ አማካሪ ዶክተር ዮሃንስ ግርማ ተናግረዋል፡፡
ክልሎች እና አጎራባች አገራት በቅንጅት ካልሰሩ ድንበር ተሻጋሪ በሽታዎችን መከላከልና መቆጣጠር እንደማይቻልም ገልጸዋል፡፡
በሽታው የስጋና የወተትን ምርትና ምርታማነት የሚቀንስ በመሆኑ ለመከላከል እንስሳትን ማስከተቡ አስፈላጊ መሆኑንም ሚኒስትር ዲኤታ አማካሪው አሳስበዋል፡፡
ለክልሎች ድጋፍ እና ለክትባት የሚሆኑ የግብዓት አቅርቦት እንደሚሰጥም በሚኒስቴሩ የእንስሳት በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶክተር ውብሸት ዘውዴ አብራርተዋል፡፡
በክልሉ የአብዛኛው ህብረተሰብ ኑሮ የተመሰረተው በእንስሳት እርባታ ላይ መሆኑ፥ ለእንስሳት እርባታ ተግዳሮት ከሚሆኑ ነገሮች አንዱ የእንስሳት ድንበር ዘለል በሽታ እንደሆን የጅግጅጋ የእንስሳት ጤና ላቦራቶሪ ሃላፊ ዶክተር ያህዬ መረኔ ተናግረዋል፡፡
እየተከሰተ ያለውን በሽታ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የክትባት ዘመቻው ላይ ክልሉ በትኩረት እንደሚሰራ መግለጻቸውን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.