Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ያሰለጠናቸውን ባህርተኞች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የባህር ኃይል ማሰልጠኛ ትምህር ቤት በመጀመሪያው ምዕራፍ ያሰለጠናቸውን የባህርተኛ ሙያተኞችን አስመርቋል፡፡
 
በስነ-ስርአቱ ላይ የተገኙት የባህር ኃይል ዋና አዛዥ ተወካይ ኮሞዶር ዋላፃ ዋቻ÷ ሰልጣኞች በውሃ ላይ የሚሰጡ ወታደራዊ ግዳጆችን በብቃት መፈፀም እንዲችሉና የባህር ሃይሉን አቅም እንዲገነቡ ስልጠናው የጎላ ሚና አለው ብለዋል፡፡
 
አገራችንን ለማፍረስ በውጭ ኃይሎች የሚጋለበውን አሸባሪውን ጁንታ ከመደምሰስ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ ባህር ሃይልን ግዳጅ የመፈፀም አቅም ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
 
በተያዘም በቢሾፍቱ ባቦጋያ ሐይቅ የ2ኛው ዙር ምዕራፍ የባህርተኛ ሙያተኞችን ስልጠና ማስጀመሪያ ፕሮግራም መካሄዱን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
በመርሃ ግብሩም ሰልጣኞች በባህር ኃይል ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የሚሰጣቸውን የወታደራዊ ባህርተኛ ስልጠና በብቃት በመፈፀም ማንኛውም ግዳጅ ለመወጣት ዝግጁ መሆን እንደሚጠበቅባቸው ኮሞዶር ዋላፃ ዋቻ ተናግረዋል፡፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.