Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው የህወሃት ቡድን በጭፍራ ግምባር ኪሳራ እየተከናነበ ነው -የግንባሩ ኮማንድ ፖስት

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሰራዊት፣አፋር ልዩ ኃይልና ሚሊሻ በጋራ በመሆን በጭፍራ ግምባር አሸባሪው የህወሓት ቡድን ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እያደረሱበት እንደሚገኙ የጭፍራ ግምባር ኮማንድ ፖስት አስታወቀ።
 
በአፋር ክልል የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የጭፍራ ግምባር የኮማንድ ፖስት አስተባባሪ አቶ አብዱ ሙሳ አሸባሪው ህወሃት በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየፈጸመ እንደሚገኝ አውስተዋል፡፡
አሸባሪ ቡድኑ የመንግስትና ግለሰብ ሃብት ዘርፏል፤ መውሰድ ያልቻለውን ደግሞ አውድሟል ነው ያሉት፡፡
በመሆኑም የአፋር ህዝብ አንድነቱን ጠብቆ አሸባሪ ቡድኑን እየመከተ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡
የአፋር ህዝብ ‘ዳጉ’ በተሰኘው የመረጃ መለዋወጫ ባህል አማካኝነት የአሸባሪ ቡድኑን እንቅስቃሴ የሚለከቱ መረጃዎችን እንደሚለዋወጥ ጠቅሰው፤ ይህም አሸባሪ ቡድኑን ለመመከት መልካም እድል ፈጥሯል ነው ያሉት፡፡
 
የአፋር ልዩ ኃይል ምክትል አዛዥ ምክትል ኮማንደር መሓመድ ሰናይ በበኩላቸው የአፋር ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ለአገሩ ቀድሞ የሚሰዋ ነው ብለዋል።
አሸባሪው ህወሃት ውጊያ በከፈተባቸው ግምባሮች ሁሉም የአፋር ክልል የጸጥታ ኃይሎች ከአገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በመቀናጀት የአገር ሉዓላዊነትን እያስከበሩ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
እንደ ምክትል አዛዡ ገለጻ፤ የአፋር ክልል የፀጥታ ኃይል ከመከላከያ ጋር በመሆን አሸባሪውን የመመከት በቂ ዝግጅት ላይ ነው።
የአፋር ክልል የሚሊሻ አባላት በበኩላቸው አሸባሪ ቡድኑን ለመዋጋት ቆርጠው መነሳታቸውን ተናግረዋል።
የሚሊሻ አባላቱ ጁንታው በአፋር ክልል ላይ ጦርነት ከከፈተበት ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ ግምባሮች ተሰልፈው ድል ሲቀዳጁ መቆየታቸውን ገልጸዋል።
በቀጣይም አሸባሪ ቡድኑ እስከሚወገድ ድረስ ከጸጥታ ሃይሉ ጎን ተሰልፈው እንደሚፋለሙ ነው ያረጋገጡት።
በሌሎች አካባቢዎች የሚገኙ የሚሊሻ አባላትም ከጸጥታ ኃይሉ ጎን ተሰልፈው አሸባሪውን እንዲመክቱ ጥሪ አቅርበዋል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.