Fana: At a Speed of Life!

የዞኑ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከድጋፍ ባሻገር ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋሞ ዞን ተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የአገር ህልውናን ለማስጠበቅ ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ የክተት ጥሪውን በመቀበል ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን ገለፁ።

በጋሞ ዞን የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሚገኙ ዘጠኝ ፓርቲዎችበአርባ ምንጭ ከተማ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ተወያይተው የአቋም መግለጫ አውጥተዋል።

የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት በጁንታው ትህነግ ቡድን ምክንያት መንግስት ተገዶ ወደ ጦርነት ገብቷል ብለዋል።

በሕዝብ የተመረጠው መንግስት ለሀገር ደህንነት ሲባል እየወሰደ ያለውን እርምጃ እና የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመደገፍ የሚከተሉትን ባለ አምስት ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል።

1. ለሀገር ደህንነትና ሠላም ሁሉም ሕዝብ ከጸጥታ አካላት ጋር በጋራ ዘብ መቆም አለበት።

2. በከሃዲው ትህነግ ቡድን ላይ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ እና ለዚህ ይረዳው ዘንድ የታወጀውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አጥብቀን እንደግፋለን።

3. በአሜሪካ መሪነት ግብጽ ፣ ሱዳን እና የተለያዩ የውጭ ሚዲያዎች እያካሄዱብን ያለውን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ዘመቻ አጥብቀን እንቃወማለን።

4. በጋሞ ዞን ያለው የተፎካካሪ ፓርቲ የጋራ ምክር ቤት የሚጠበቅበትን ሁለንተናዊ ድጋፍና ተሳትፎ ከማድረግ ባሻገር የክተት ጥሪውን በመቀበል ለመዝመት ያለንን ዝግጁነትና ፍቃደኝነት እንገልጻለን።

5. መንግስት እየወሰደ ያለውን ሕግን የማስከበር እርምጃዎች እንዲሁም የኮማንድ ፖስትን ተግባር በተጣረሰ የሚወሰዱ የፖለቲካ ፣የማህበራዊና የኢኮኖሚ ስውር የሆኑ አሻጥሮችን አጥብቀን እንቃወማለን ።

የጋሞ ዞን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የኢትዮጵያን ሰላምና ክብር ለማስጠበቅ ሁለንተናዊ ድጋፍ ለማድረግ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን የጋሞ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያደረሰው መረጃ ያመላክታል።

በማቴዎስ ፈለቀ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.