Fana: At a Speed of Life!

አንዳንድ ምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ኢትዮጵያን እንደ ሉዓላዊ አገር እየቆጠሯት አይደለም – ላውረንስ ፍሪማን

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካዊው የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ተንታኝ ላውረንስ ፍሪማን የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ኢትዮጵያን እንደ ሉዓላዊ አገር ከመመልከት እና ሚዛናዊ ዘገባ ከመዘገብ ይልቅ የምዕራባውያኑን ፍላጎት በዘገባዎቻቸው እያንጸባረቁ እንደሚገኙ ገለጸ፡፡

እንደ ሲ ኤን ኤን፣ ኒውዮርክ ታይምስ፣ ዋሽንግተን ፖስት፣ ቢቢሲ እና የመሳሰሉት መገናኛ ብዙኃን ነጻ ሚዲያዎች ሳይሆኑ በምዕራባውያን መሪዎች እና የጂኦ ፖለቲካ ዘዋሪዎች ፍላጎት ላይ ጥገኛ ሆነው ኢትዮጵያ ላይ የሀሰት ዘገባ እየሰሩ የሚገኙ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ላውረንስ ፍሪማን ÷ መገናኛ ብዙኃኑ ኢትዮጵያውያኑ መሪያቸውን እንደመረጡና አገሪቷ ሉዓላዊ አገር እንደሆነች ሊገነዘቡ ይገባልም ነው ያሉት።

የፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ተንታኙ አሸባሪው ቡድን በመረጠው ምርጫ መሰረት እርምጃ እየተወሰደበት እንደሚገኝም ሚዲያዎቹ እንዲገነዘቡ እና በህዝብ የተመረጠ ሉዓላዊ መንግስት ባላት አገር ላይ የተንሸዋረረ ዘገባ ከመስራት እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡

አያይዘውም ምዕራባውያኑ እና የአሜሪካ ምክር ቤት አባላት ስለ አፍሪካ ጉዳዮች እንዲሁም ስለ ኢትዮጵያ አነስተኛ እውቀት እንዳላቸው ጠቁመዋል።

የአሜሪካ ምክር ቤትና የባይደን አስተዳደር ለአሸባሪው ቡድን የሚያደርጉት ድጋፍ በአፍሪካ ቀንድ የሚያሳርፈውን አደገኛ ፖለቲካዊ ተጽዕኖ እንደገና ከግምት ውስጥ አስገብተው ከኢትዮጵያ ጎን እንዲቆሙ ጠይቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ እየተጫወተች የምተገኘውን የላቀ ሚና አሜሪካ ከግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርባታልም ነው ያሉት ከአዲስ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.