Fana: At a Speed of Life!

በምዕራብ ሸዋ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ የሸኔ አሸባሪዎች ተደመሰሱ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በተካሄደው ኦፕሬሽን በመቶዎች የሚቆጠሩ የሸኔ አሸባሪዎች ሲደመሰሱ በርካቶች ደግሞ መማረካቸውን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት እንዳስታወቀው፥ ከጥቅምት 2 እስከ ህዳር 8 ቀን 2014 ዓ.ም በፌዴራል ፖሊስ፣ በኦሮሚያ ልዩ ሃይልና በኦሮሚያ ሚሊሻ በጋራ በተካሄደው ኦፕሬሽን በተለያዩ የዞኑ ወረዳዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የአሸባሪው ሸኔ ቡድን አባላት ተደምስሰዋል።
በምእራብ ሸዋ ስር በሚገኙ በዳኖ እና ጅባት ወረዳዎች 63 ታጣቂዎች፣ በአምቦ ወረዳ 47፣ በአቡነ ግንደ በረት 235፤ በጥቅሉ 345 ታጣቂዎች እርምጃ ተወስዶባቸዋል። ከእነዚህ ውስጥ አራቱ የአሸባሪው የጦር መሪዎች መሆናቸው ታወቋል።
በርካታ ቁጥር ያለው የአሸባሪው የሸኔ ሃይል ቁስለኛ የሆነ ሲሆን በርካቶችም እጃቸውን ለፀጥታ አካላት ሰጥተዋል።
ከዚህም በተጨማሪ በርካታ የጠላት ቡድኑ ሰርጎ ገቦችና ሰላዮች ተይዘዋል።
ሰላማዊ መስለው በህበረተሰቡ ውስጥ ለመደበቅ የሞከሩ የአሸባባሪው የሸኔ አባላት በህዝቡ ጥቆማና ከፍተኛ ተሳትፎ እየተለቀሙ እንደሚገኙ ነው የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ያስታወቀው።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.