Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ የቡና ምርምርና ልማት ሲምፖዚየም መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሀገር አቀፍ የቡና ምርምር እና ልማት ሲምፖዚየም ዘላቂ የቡና ልማት እና የእሴት ሰንሰለት በሚል መሪ ቃል በዲላ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ችሮታው አየለ የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ያላቸው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

አያይዘውም ቡና የሀገራችን የኢኮኖሚ ዋልታ እንደመሆኑ ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት የራሳቸውን ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ አቅርበዋል::

የሳይንስና ከፍተኛ ትህምርት ሚኒስቴር ተወካይ ዶክተር እሸቱ ከበደ በበኩላቸው፥ ቡናን በጥናትና ምርምር ላይ በመመስረት አዳዲስ እውቀቶችንና ቴከኖሎጂዎችን በማምጣት የሕብረተሰቡን ብሎም የሀገርን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አቅም ማሳደግ ይገባል ብለዋል።

ሲምፖዚየሙን የዲላ ዩኒቨርሲቲ፣ የጌዲኦ ዞን እና የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በጋራ ያዘጋጁት ሲሆን በሲምፖዚየሙ የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚረዱ ጥናታዊ ጽሁፎችም ይቀርባሉ።

ሀገር አቀፍ የቡና ምርምርና ልማት ሲምፖዚየሙ ለሁለት ቀናት እንደሚቆይ የደቡብ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዘገባ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.