Fana: At a Speed of Life!

ህንድ በባህር ዘራፊዎች በደረሰ ጥቃት 20 ዜጎቼ ታፍነው ተወሰዱብኝ አለች

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 7፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ህንድ በምዕራብ አፍሪካ የውሃ አካል የነዳጅ ዘይት ጭኖ በመሄድ ላይ በነበረ መርከቧ ላይ  በተፈፀመ ጥቃት 20 ዜጎቿ  ታፍነው እንደተወሰዱባት አስታወቀች፡፡

መርከቡ ከአንጎላ ወደ ቶጎ ዋና ከተማ ሎሜ የነዳጅ ዘይት ጭኖ በመሄድ ላይ እያለ ጥቃት እንደደረሰበት ተነግሯል፡፡

የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር÷ 20 ዜጎች በምዕራብ አፍሪካ የባህር ላይ ዘራፊዎች ታፍነው መወሰዳቸውንና ይህ ችግር በአካባቢው እየተባባሰ መምጣቱንም ገልጿል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በናይጄሪያ አቡጃ ያለው የሀገሪቱ ኤምባሲ ከናይጄሪያ ባለሥልጣናት እንዲሁም ከጎረቤት ሀገራት ባለስልጣናት ጋር መወያየታቸውን  አስታውቋል፡፡

መርከቧ በባህር ላይ ዘራፊዎች ጥቃት የደረሰባት ከቱጎ ዋና ከተማ ከሎሜ የባሕር ዳርቻ በስተ ደቡብ ምስራቅ 213 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ዩኒየን የባህር ሃይል የተባለ የመርከብ ባለቤት እና አንቀሳቃሽ በድረ ገጹ ባሰፈረው ፁሁፍ የነዳጅ ዘይቱን ጭኖ ሲጓዝ የነበረው መርከብ ጥቃት እንደተፈፀመበት በማረጋገጥ  ኩባንያው ችግሩን ለመፍታት  ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለስልጣናት ጋር እየሰራ መሆኑን ነው የገለፀው፡፡

የመርከብ ኢንዱስትሪው÷ ከቅርብ ጊዜ  ወዲህ በተለይም  በጊኒ ባሕረ ሰላጤ እና  በናይጄሪያ ዙሪያ የባህር ዳርቻዎች የባህር ላይ ጠለፋ ክስተቶች እየጨመሩ መምጣታቸው ተጠቁሟል፡፡

ምንጭ፡-አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.