Fana: At a Speed of Life!

ለ39ኛው የአፍሪካ ህብረት አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ የሀገራት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገብተዋል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በ39ኛውን የአፍሪካ ህብረት አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ ለመካፈል የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ወደ አዲስ አበባ ገብተዋል።

በ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የኮትዲቯር፣ የጋቦን እና የቡርኪናፋሶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ቀደም ሲል አዲስ አበባ መግባታቸው ተገልጿል።

ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የበርካታ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ተወካዮችም አዲስ አበባ ገብተዋል።

በዚህ መሰረት ትናንት ምሽት የሶማሊያ፣ የቻድ፣ የሞዛምቢክ፣ የደቡብ አፍሪካ፣ የማላዊ፣ የታንዛኒያ፣ የአንጎላ፤ የናይጄሪያ ፤ የቶጎ፣ የኮሞሮስ፣ የቤኒን፣ ናሚቢያ፣ ጂቡቲ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ እና የዛምቢያ የውጭ ጉዳይ ተወካዮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካዮች ናቸው አዲስ አበባ የገቡት።

39ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ ለሁለት ቀናት በዋነኛነትየሚመክረው “ጥበብ፣ ባህልና ቅርስን የምንፈልጋትን አፍሪካ ለመገንባት እንጠቀምባቸው” በሚል መሪ ሃሳብ ነው።

በአህጉሪቱ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክር ይጠበቃል።

በወቅቱም የፕሮቶኮል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል አቶ ፌይሰል አሊይ በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.