Fana: At a Speed of Life!

መገናኛ ብዙሃን አገር ለመገንባት የጀመሩት ተግባር ሊያጠናክሩ ይገባል- ዶክተር ጌታቸው ድንቁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መገናኛ ብዙሃን በአገራዊ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠርና ያደገች አገር ለመገንባት የጀመሩትን ተግባር ማጠናከር እንደሚገባቸው የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ ተናገሩ፡፡
ዶክተር ጌታቸው በድሬዳዋ አስተዳደር ለመገናኛ ብዙሃንና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች በተዘጋጀው የክህሎት ማዳበሪያ የሥልጠና መድረክ በዘርፉ ዙሪያ ትምህርት ሰጥተዋል።
በወቅቱ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ በአሁኑ ወቅት ከመገናኛ ብዙሃን አንድነትን የማጽናት ተግባርን ጨምሮ በርካታ ሥራዎች ይጠበቃሉ።
ለሁሉም የምትበጅ አገር በመገንባት ተግባር ሁሉም ዜጋ የድርሻውን እንደሚወጣ መገናኛ ብዙሃን በሙያቸው ሚናቸውን ሊጫወቱ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
‹እንደ ከዚህ ቀደም አንዱ በሌላው ላይ ድንጋይ የሚወራወርበት ጊዜ ሣይሆን መገናኛ ብዙሃኑ ራሱ ተለውጦ ሌላውን መለወጥ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት አለበት ብለዋል፡፡
መገናኛ ብዙሃን በአስተሳሰብ፣ አገር በመውደድና በማስቀደም፣ በመወያየትና የጋራ አስተሳሰብ አንጥሮ መሰረታዊ የዴሞክራሲ መርሆዎች በራሳቸው ውስጥ መጀመር አለባቸው ሲሉ ጠቁመዋል፡፡
እንደ ዶክተር ጌታቸው ማብራሪያ፤ መገናኛ ብዙሃን ለአገር የሚበጁ አጀንዳዎችን እየቀረጹ በራሱ የሚንቀሳቀስና ለችግሮች ደረጃ በደረጃ መፍትሄ ለመስጠት የሚተጋ ማህበረሰብ ለመፍጠር መስራት አለባቸው።
መጪው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ የተሳካ እንዲሆን በማገዝ በኩልም ያለበትን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ከወዲሁ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡
መገናኛ ብዙሃን አገራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ከሥራ አስፈጻሚዎች ተፅዕኖ እንዲላቀቁ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን አመልክተው÷ “ነጻነትን ማቀዳጀት ተገቢ ነው” ብለዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.