Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ ለሰራዊቱ እና ለተፈናቃዮች 5 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የአይነት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለመከላከያ ሰራዊት እና ለተፈናቀሉ ወገኖች 5 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የአይነት ድጋፍ አድርጓል።
 
ድጋፉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ÷ ዛሬ በጋሸና ግንባር በመገኘት ለመከላከያ ሰራዊት፣ ለአማራ ልዩ ሃይል፣ ፍኖ እና ሚሊሻ አስረክበዋል።
 
የተበረከተው ድጋፍ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስር ከሚገኙ ተጠሪ ተቋማት፣ ከሰራተኞች ደመወዝ፣ ከሚሲዮኖች እና ከአምባሳደሮች የተገኘ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዋ ተናግረዋል፡፡
 
የተደረገው ድጋፍም የህጻናት አልሚ ምግብ፣ የንጽህና መጠበቂያ፣ 54 ሰንጋዎችን እና ሌሎች የአይነት ድጋፎችን ያካተተ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
 
ድጋፉ ለመከላከያ ሰራዊት አባላት እና በህወሓት የሽብር ቡድን ሃብት ንብረታቸው ለወደመባቸው እና ለተፈናቀ ዜጎች የሚውል መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አንስተዋል፡፡
 
የግንባሩ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች በበኩላቸው÷ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚሰራቸው የዲፕሎማሲ ስራዎች ባለፈ ግንባር ድረስ በመምጣት ሰራዊቱን ማበረታታቱ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል።
 
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰራተኞች፣ የኢትዮጵያ ስትራቴጂክ ኢኒስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች ኤጀንሲ እና ታዋቂ አርቲስቶች በጋሸና ግንባር ተገኘተው ሰራዊቱን አነቃቅተዋል።
 
በምንይችል አዘዘው
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.