Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በተለያዩ አካባቢዎች የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አከናወኑ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር እና የሰላም ሚኒስቴር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አከናውነዋል፡፡

የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሰራተኞች እና አርሲ ዞን መርቲ ወረዳ ነዋሪዎች የችግኝ ተከላ መርሐ ግብርን ሲከናወን ኢንጂነር አይሻ መሀመድ እና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ዶክተር ዓለሙ ስሜ ተሳትፈዋል።

ከችግኝ ተከላው በተጨማሪ 600 ለሚሆኑ አቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት መርጃ መሳሪያ ቁሳቁስና ለ21 አርሶ አደሮች ደግሞ የዉሃ ፓምፕ በሚኒስቴርሩ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

በተመሳሳይ የሰላም ሚኒስቴር ከእስራኤል ኤምባሲ ጋር በጋራ በመሆን በእስራኤል ኤምባሲ  ቅጥር ግቢ የችግኝ ተከላ  መርሐ ግብር አካሄደዋል፡፡

በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም የኢትዮጵያና የእስራኤል መንግስት ወዳጅነት የረጅም ጊዜ ታሪክ ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

ሁለቱም ሀገራት በጋራ በመሆን በልማትና በሰላም ግንባታ ስራዎች አብረው ሲሰሩ ቆይተዋል ፤ አሁንም እየሰሩ ይገኛሉ ሲሉም ተናግረዋል፡፡

እስራኤላዊያን እንደ ኢትየጵያ በችግኝ ተከላ ልምድ ያላቸው  መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ ፥ አረንጓዴ አሻራችንን በጋራ ማሳረፋችን ያለንን ቅንጅት ለማጠናከር ያግዛል ማለታቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.