Fana: At a Speed of Life!

ሱዳን ጎርፍ ባስከተለው አደጋ ምክንያት የሦስት ወር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጇን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሱዳን የፀጥታና የመከላከያ ምክር ቤት ሀገሪቱ ጎርፍ ባስከተለው አደጋ ምክንያት የሦስት ወር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጇን አስታውቋል፡፡

በሱዳን በዚህ ዓመት በጎርፍ ምክንያት የ99 ሰዎች ህወት ማለፉን የሀገሪቱ የዜና አውታር ዘግቧል፡፡

እንዲሁም 46 ሰዎች የተጎዱ ሲሆን ከ100 ሺህ ቤቶች በላይ ወድመዋል፡፡

የውሃና የመስኖ ሚኒስትሩ በዚህ ዓመት የአባይ የውሃ መጠን በ17 ነጥብ 57 ሜትር ከፍ ማለቱን ተናግረዋል፡፡

ይህም መመዘገብ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በዚህ መጠን የአባይ ውሃ ከፍ ያለ ማለቱን ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

አሁንም ቢሆን የዝናብ መጠኑ እየጨመረ በመሄዱ ከፍተኛ ጉዳት እንዳያስከትል ስጋት ፈጥሯል፡፡

ምንጭ፦ሲጂቲኤን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.