Fana: At a Speed of Life!

ሳዑዲ የኮቪድ19 ክትባት ያልወሰዱ ምዕመናን ወደ መካ እንዳይገቡ ከለከለች

አዲስ አበባ፣ መ ጋቢት 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ታላቁ መካ መስጊድ (አል-መስጂድ አል-ሀራም) የጸሎት ቦታ የሚያቀኑ ምዕመናን የኮቪድ19 ክትባት የተከተቡ ብቻ መሆናቸውን አስታወቀች፡፡

የሃጅና ዑምራ ሚኒስትሩ ውሳኔው ከረመዳን የጾም ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ነው የገለጹት፡፡

ውሳኔው ከሃጅና ዑምራ ተጓዦች በተጨማሪ ፀሎት (ሶላት) የሚያደርጉትንም ያካትታል ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ ሁለተኛ ዙር ክትባት የወሰዱት በቀጥታ መግባት እንደሚችሉም ገልጸዋል፡፡

አንደኛ ዙር የወሰዱት ደግሞ ከ14 ቀናት በፊት የተከተቡ መሆን እንደሚገባቸውም ነው የገለጹት፡፡

በ2019 እስከ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ምዕመናን በሐጅና ዐምራ ጸሎት የተሳተፉ ሲሆን፥ ባለፈው ዓመት ደግሞ በሳዑዲ የሚኖሩ 10 ሺህ ሙስሊሞች መሳተፋቸው ይታወሳል፡፡

በሳዑዲ እስካሁን 393 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 6 ሺህ 700 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

34 ሚሊየን ሕዝብ ያላት ሳዑዲ ከ5 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ዜጎቿ ክትባት መሰጥቷን ገልጻለች፡፡

 

ምንጭ፦ አልጀዚራ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.